ብያሬድ ሕሉፍ
ዘመድ የለ ፈጥኖ ደራሽ
የሚያበረታታ
በተዘጋ ቤት ፍርስራሽ
ውሀ የለ ሚበላ ቁራሽ
መኖር ግድ ሆኖ ሥጋ ለባሽ:
ቀን እስኪያፍ እስኪመሻሸ:
ባለኣደራ ኣትክልት: ማሙሽ
ባፈራ እንዴት ደስ ባለኝ : ደም መላሽ::
ይሄው ለዓመታት ስመኝ ሳይታክተኝ ሳይደክመኝ ምን እለ ቢያድለኝ ለተከፍው ልቤ! ማፅናኛ ደብዳቤ:
ጌታ ልጅ ቢስጠኝ: ከሚታመን ጏድ ከሚወደኝ ኣለሁ ባይ ሲከፋኝ:
ደስታዬም ተካፍይ : ልጅ ካለም ተንከባካይ:: በዓለም ከዚህ በላይ ምን ኣለ ሌላ ንዋይ::
ታድያ ስኖር ስንገላታ ስወጣ ስወርድ በርካታ ካሳስብኝ ሁኔታ: መለስ ብሎ ጌታ
ተስፋ እንዳልቆርጥ እንድበረታ: ስመፕው ውሎ ያደረ:
ባለውለታ ባል: ጌታ ወረወረ: መህፀኔም ቆጠቆጠ መሀን ሁኖ ኣልቀረ: የበቀለ ልጅም: ስመፕው ተባለ:: አድጎምእጅ ስነዘረ:
ለተከፋው ሁሉ አጥቶት ለነበረ ውሀ ምግብ ላቅብ ኣለ
ጉልበት እስከቻለ::
መሳቅ ኣይሉት ገደብ የለሽ ሳቀ ፍፁም በደስታ ልቤ ፈነደቀ: ፍትሕ መሬት ላይ ፀደቀ::
በዚያው ልክም ምቀኛ ፈለቀ ከወሀ ጥም ድሀን ላላቀቀ ወነጄለው ጉሮሮው እንዳደረቀ: እርር ድብን ብሎምበንዴት ደቀቀ:
ግራ ቅኝም ተቻኮለ
ልጄን ሊያጠፋ ምን ግዜ ኸጀለ::
ታድያ በጠማማ አእምሮ ኣምባጏሮ ጭሮ
ንፁሃን ገደለ ልጄንም ጨምሮ:: ላያልቅ የኔ እሮሮ!
ወይ ዘንድሮ!
መቼ ያልቃል ተነግሮ
ቀማኛ ካልተመቸው ኑሮ
አቅመ ቢሱን ስባብሮ
ልበ ቁኑን አጭበርብሮ
ሁሉ እንዲጠፋ ተበነቃቅሮ ይራራጥ ጀመረ በአስተክሮ: የአህያዋን ምሳሌ ተክትሎ:
“እኔ ከሞትኩኝ በኃላ
ስርዶ አይብቀል እንኻን የሚበላ“,
የበቀለ ጨቅላ..
ስመኘው ሞኝ ተላላ!