ኢትዮጵያ ለሺ ዓመታት ስታንቀላፋ! Ethiopia:

News

ኢትዮጵያ ለሺ ዓመታት ስታንቀላፋ!

Ethiopia: Thousand years in deep sleep!

ተስፋፊ ቀማኛ

እንካንስ ሌላ ስው ቀርቶ

ራሱም በሰላም ማይተኛ

ራስ ጠል በሽተኛ

ልክፍት ኣይሉት ጤነኛ

የግዜ ጉዳይ  ሆነና

መሠፈሩ ላይቀር

በሠፈረው ቁና።

እብድ ውሻ

ሲኮበልል ውሎ ማምሻ

ኣብሮ ኣደግ የቤት ልጅ

የጌታውም እጅ

ቆርጦ ሚበላ ባደገበት ደጅ።

ተስፋፊ ቀማኛ

ይቅር ማይል ምንቀኛ

ዓን ጨፍኖ ኣሽጎ ውስጥ ጓሮ

በጫጫታ ጀሮን ኣደንቁሮ

እንዳይፅፍ እንዳይማር

የኃሊት  ኣዙሮ

የስው እጅ በሰንሰለት ኣስሮ፣

ኣኮላሽተው ስነኣ እምሮ

ኣደህይቶ ሰባብሮ

መስሎት እድሜ ልኩን

በቁንጦት  ሚኖር ኣሳምሮ።

ዙሮ ዙሮ ይህ ስንዛሮ

ሳያውቀው ኑሮ

ባጠመደው ቅርቅርት

መውደ ተሸንጥሮ።

ሠርፃ  ድንግል ሲኮበልል ከኣንኮበር ደጅ

መናገሻው ባሕር ጣና (ኢንፍራዝ) ሊያደራጅ

ዛጉየዎችን ኮምኩሞ፣ ቅማንትን ሊፈጅ

ሊያቃጥል በሳት ነዳጅ።

ይህ ኣልበቃ ብሎ ስስንዮስ ሲተካ

እርኩስ ሥራውን ተግባሩ ግቡን ሊያረካ።

ቡልጋን ጥሎ ጎንደር ሲቀዳጅ

ይህን ሊያስናጅ

ሃይማኖቱን ክዶ ሳይሆን በግዳጅ

ካቶሊኮች ስወዳጅ

ያለምክንያት ኣይደል

ፈልጎ ነው እንጂ ተጨማሪ ኣጋዥ እጅ

ቅማንትን ሊል ቦጫጭቆ እንደ ቅዳጅ።

ነገሩ ሳይሆን

ለምን ካቶሊኮች ኣስተናገደ

ሃይማኖቱንም ካደ።

እምነት የግል ሲሆን፣

ሰዉ እንደወደደ፣

መብቱ እንደተጠበቀ

ሕግ ያስተናገደ፣

ኣጠያያቂው፣ ክህደቱ ለመፈፀም በዘፈቀደ

ለምን ተገደደ?

ቀጠል ብሎ መጣ

ፋሲል ሱስንዮስ የቡልጋ ተወላጅ

ቦርቹጋሎች ተጠቅሞ ጎንደር ሲቀናጅ

እሱም እንደ ድመት ልጅ:

(“ወዲድሙኣይገድፍ ግብረ እሙ”

እንደሚባለው ትርክት)

ህንፃውን ካበጁ

ኣባሪራቸው ከደጁ

ምንም እንዳልበጁ።

ይህ ነው ባጭሩ

ያኮበር፣ ቡልጋ ታሪክ ምስጥሩ

እንዳትሳሳቱ

በጌምድር ብሎ ጎጃም ከጥንቱ

መሬቱ ንብረቱ

ያንኮበሮች ኣልነበረም መሡረቱ ።

ኣሳፋሪው ነገር ፣ ኣስከፊው ነውሩ

የሰለሙን ነገድ ነን ብለው ሰፎክሩ፣

ሙልጭ ያለ ቅጥፈት ሲያወሩ፣

እየተንጠራሩ።

የኣንድ ቤተ ስብ ዘር

የጎሳም ኣይደል፣ ስብስብ የጎጥ ወይ መንደር

የይኩኖ ኣምላክ ብቻ ደም ሥር

ለመቶ ዓመታት መንግሥትነትን ሲቆጣጠር

ሃገሩትዋ ጀመረች ማሽቆልቆል የኃላ ኃሊት መዞር።

ለዚህ ነው ፀሃፊዎች ሲተርኩ በይፋ

“ኢትዮጵያ ለሺ ዓመታት ስታንቀላፋ

ዓለም ረስቶኣት ቆርጦ ተስፋ፣

እርስዋይ ትርክቱም ተቀብላ፣

ዓሜን ብላ፣

ትርክቱ እዉን ሃቅ ሆኖ ፣

እንደ ድንቅ ተዋናይ ገኖ

ከኣጥናፍ እስክ እጥናፍ ተስፋፋ፣

ሀገሩትዋም ተምሳይ ቦጅቦጅ ኣረፋ።

ምንጭ

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Fasilides

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Sarsa_Dengel 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *