የበቀለ ጨቅላ.. ስመኘው ሞኝ ተላላ!
ብያሬድ ሕሉፍ ዘመድ የለ ፈጥኖ ደራሽ የሚያበረታታ በተዘጋ ቤት ፍርስራሽ ውሀ የለ ሚበላ ቁራሽ መኖር ግድ ሆኖ ሥጋ ለባሽ: ቀን እስኪያፍ እስኪመሻሸ: ባለኣደራ ኣትክልት: ማሙሽ ባፈራ እንዴት ደስ ባለኝ : ደም መላሽ:: ይሄው ለዓመታት ስመኝ ሳይታክተኝ ሳይደክመኝ ምን እለ ቢያድለኝ ለተከፍው ልቤ! ማፅናኛ ደብዳቤ: ጌታ ልጅ ቢስጠኝ: ከሚታመን ጏድ ከሚወደኝ ኣለሁ ባይ ሲከፋኝ: ደስታዬም ተካፍይ : ልጅ ካለም ተንከባካይ:: በዓለም ከዚህ በላይ ምን ኣለ ሌላ ንዋይ:: ታድያ ስኖር ስንገላታ ስወጣ ስወርድ በርካታ ካሳስብኝ ሁኔታ: መለስ ብሎ ጌታ ተስፋ እንዳልቆርጥ እንድበረታ: ስመፕው ውሎ ያደረ: ባለውለታ ባል: ጌታ ወረወረ: መህፀኔም ቆጠቆጠ መሀን ሁኖ ኣልቀረ: የበቀለ ልጅም: ስመፕው ተባለ:: አድጎምእጅ ስነዘረ: ለተከፋው ሁሉ አጥቶት ለነበረ ውሀ ምግብ ላቅብ ኣለ ጉልበት እስከቻለ:: መሳቅ ኣይሉት ገደብ የለሽ ሳቀ ፍፁም በደስታ ልቤ ፈነደቀ: ፍትሕ መሬት ላይ ፀደቀ:: በዚያው ልክም ምቀኛ ፈለቀ ከወሀ ጥም ድሀን ላላቀቀ ወነጄለው ጉሮሮው እንዳደረቀ: እርር ድብን ብሎምበንዴት ደቀቀ: ግራ ቅኝም ተቻኮለ ልጄን ሊያጠፋ ምን ግዜ ኸጀለ:: ታድያ በጠማማ አእምሮ ኣምባጏሮ ጭሮ ንፁሃን ገደለ ልጄንም ጨምሮ:: ላያልቅ የኔ እሮሮ! ወይ ዘንድሮ! መቼ ያልቃል ተነግሮ […]
Continue Reading