እስካለሁ በሕይወት
ሆዴን ባር ባር አለው ልቤ እንዲያ ሊረበሽ
ሰክሮ እንዳደረ ሰው ሆዴን ሲቅለሸለሽ
ናፍቆቱን አልቻልኩም ትግራይ እንዴት አለሽ?
እኔ ለኔ ብዬ መኖርን ሳልጀምር
አበሳ ስንቆጥር በጠላት ወታደር
ለነጻነትሽ ልሞት ወረድኩኝ ከገጠር
ተበደልሽ ብዬ እንዲያ ስጮህልሽ
ሁሉም እንዳላየ ፊቱን አዞረብሽ፤
የቁም እስረኛሽ ነኝ ኮከብ ገዳይ ጥሎሽ
ምንም አይታክተኝ ላንቺ ብሞትልሽ።
ከጎንሽ አድሪጊኝ ጠረንሽ ካለበት
ዘብ እንድሆንልሽ እስካለሁ በህይወት።
ትእዛዝ ቢተወደድ