ካዱሽ ወይ?

News

ካዱሽ ወይ?

አንድ የነበሩ … በአንድ እቅፍ የሰሩ
ከኣብራክሽ ወጥተው … ባንቺ ስም የማሉ
የተሰዉ ላንቺ … የቆሰሉ ለክብርሽ …
… በስምሽ የማሉ … ሊያስከብሩ ለሉዐላውነትሽን
ሊያስመልሱ … የተወረረውን ግዛትሽን
የፎከሩ … ያስፎከሩ
የዘፈኑ … ያስዘፈኑ
ካዲሽ ወይ?

አስመለሱ ወይ … ክብርና ሞገስሽን
ወይስ በስምሽ … ተደራደሩ?

… ልጆችሽ ዳያስፖራዎች ..
ጮክ ብለው … መፈክር ሲያሰሙ …

Amhara forces … out of Tigray!
Eritrean forces … out of Tigray!
Abyi Ahmed …to ICC!
Isayas Afewrki … to ICC!

ልባቸው ተሰበሮ …ተስፋቸው ተሟጦ
ሲያንኳኩ የምእራባያውንን ፓርላማ … ሲጎበኙ ኮንግረስን
ሲጻፉ ደብዳቤ … ትግራይ እንድትሰማ … በአለም በሃያላን

… ግን ካዱሽ ወይ ልጆችሽ … እቅፍሽ ላይ ያሉ
እኔ እኔ ብለው … ለስልጣን ሲሻሙ

… ካዱሽ ወይ ? ካዱሽ ወይ? ካዱሽ ወይ?

መታሰቢያነቱ ለተካደቸው የትግራይ እናት ይሁን
ኢዮብ ግደይ 28 August 2024

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *