ጭንቅላተ ቢስ!

News

ጭንቅላተ ቢስ!

ማስብ ማስተንተን
ጨርሶ የተሳነው ኣንጎለ ቡኩን
እጅ እግር ኣልባ
ሃገር ይቅር
መንደር ማስተዳደር
ፈፅሞ ማይችል
ሆድ ፍቅር ያሳበደው ጅል
ግብዝ ድንብርብር።

ኣላስፈለገ ፀረ-ሃገር ክብር
ሚደራደር
ኣምስት ወደብ
ልጥራቸ በክምር፣
ባፅዕ- ኣዶሊስ
ዙላ- ማሳዋ-
ጅቡቲም – ጭምር
ለባዕድያን ሲቸረችር
መስሎት ሊያንበረክክ
ትግራይን ለመጉዳት።

ኣርቆ ኣለማስብ
ዓይን ያለው ዓይነ ሥውር፣
የምንቀኛ ነገር
ቂም ብቀል ኮትኩቶ ሚቀለብ
ራስ ወዳጅ ውዥምብር።

በሠራው እኩይ ተግባር
ተፀፅቶ እንደማለት በሉኝ ይቅር
ንሣሄ እንደመግባት ሚቆጥር እንደነውር።

ባጠፋው ሳይቀጣ
መልሶ ኣይን ኣውጣ
ኣሁን ወደብ ይምጣ
ብሎ ማፍጨርጨር ጣጣ
እስቲ ምን ይባላል ምንስ ብሎ ይነገር
በሰራሀው ጣጣ ባነፅከው መቃብር
ራስህ ስትቀበር
ስትገባ ገደል
ኣሁን ኣንተን ማን ይከተል።

ደግሞም ኣለማፈር
ባልዋለበት ተግባር
ሌላ ስው መወንጀል
እየ! ያንተ ኣመል
ኣየ! ያንተው ተንኮል
በሰው ያጠመድከው
ራስክን ሲፈነግል።

ማን ይዘንማን ይልቅስ
ምንስ ድንካን ይትከል
ኣንተው በፈጠርከው ትርምስ
ሊሸኚህ በግርግር ማዕበል።

ተመስገን ኸበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *