ወሮበላ!

Poems

(በተመስገን ኸቨደ) –

ወሮበልላማ ወሮበልስ ነው
አያስገርም ባጋጣሚ
ቁራኛ መንገድ ላይ ብታገኘው
ተከታይ ማፍራቱ ነው ምያስደምመው:
ይህ ነው ግዜ ስበላሽ እምለው።

የወሮበላ ነገር ተነግሮም ማያልቅ
ወሃ ቅዳ ዋሃ መልስ
ይመስል ፍትሕ ያነግስ
አጥፊዎች በይቅርታ ከሥር ሲለቅ:
የተተፋው ምራቅ ገና ሳይደርቅ
ካርቸሌው ጭንቅንቅ ድብልቅልቅ
በቂም በቀል የታሠሩት ለማድቀቅ::

ወሮበላ ፈላጭ ቆራጭ
ንጉስ ነገስት አልጋ ላይ ተቀማጭ
አዋቂ ፈላስፋ ፈላጊ አዳማጭ
እሙን ዜጋ ፍጽም ጭራሽ
እኔ ነኝ ባይ ተሞጋሽ:
ሆኖ ሲቀርብ : አታላይ
ምን መኖር ደስ ይላል
በዚች አለም ላይ።

ወሮበላ ግዚያዊ ጥቅሙን ሲያራርጥ
ሐገር ሲሽጥ ሲለውጥ:
ጅቡቲ በል ባሕረ ነጋሽ:
ያገር አካል ያገር ቁራሽ:
ለማርያትሬዛ በርካሽ
ስው ታጥቶ ደም መላሽ:
ሐገር ስትበላሽ::

ይህ ወሮበላ
ጥቅምም የለው መላ
ሲርበው የራሱ ወገን ዘልዝሎ ሚበላ፡
አዝሮ ማስብ ምይችል
ጭንቅላት የለው ደሮን ያክል:
ትናንት የሽጠው ሐገር በውል
መልሶ በኃል ልንጠቅ የሚል፡
እፍረት የለው ቅንጣት
ስለሌሎች ማንነት አውቅ ባይ
ተገትሮ አደባባይ
ከተጠያቆቹ በላይ።

የስው መብት ማያከብር
በሆነው ባልሆነው ሚዳፈር
መሪ ሆኖ ሐገር ሲያስተዳድር
ዳኛ ሆኖ ፍትሕን ሲያደናብር
ሆኖ መምሕር
ድንቁርናን ሲያስተምር
እግዚአኦ ምንታምር!
ሰውረነ ስውር
ከማአቱ!
ደምረነ ደምር
ከምሕረቱ!
ምእንተ ሐገሪቱ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *