ማን ብለን አንጥራቸው?

Poems

ከጡዑመ ልሳን፡ አድማሱ

{የዚህ ርእስ፡ ኢላማ የሚያነጣጥረው
የዚህ እኩይ ተግባር ፈፃሚ/አስፈፃሚ በሆኑት ብቻ ነው፡}

እስከ ማእዜኑ?

እስክ ማእዜኑ፡ ህዝብ እሚታመመው፡ በርሃብ የሚያልቀው፡
እስከ ማእዜኑ፡ ስልክ ሚታገደው፡ መብራት ሚቅዋረጠው፡

እስከ ማእዜኑ፡ ህጻናት የሚያልቁት፡ እናቶች በወሊድ ሚሞቱት፡
እስክ ማእዜኑ፡ መንገድ የሚዘጋው፡ ባንኮች፡ የማይሰሩት፡

ጦርነት አውጆ፡ በርሀብ፡ በህመም፡ ህዝብን የማምከኑ፡
ካላንዳች መፍትሄ፡ ካላንዳች መቅዋጫ፡ እንዲህ የሚኮነው፡ እስከ ማእዜኑ?

የዚህ ሁሉ ችግርና ፍዳ፡ መቸነው ማብቂያና መቅዋጫው፡
ጭንቁ፡ ረገብ ብሎለት፡ ህዝብ እፎይ የሚለው፡
የጥፋት ዘመቻው ቆሞ፡ መከራው፡ አባርቶ፡ ሰላም የሚሰፍነው፡
ከበባው ተሰብሮ፡ ርሀብ ቸነፈሩ፡ ሰቆቅዋው የሚያልቀው?

ሰው በሰውነቱ፡ ህዝብ በህዝብነቱ፡ ፍርድ የሚሰጠው፡ ፍትህ የሚያገኘው፡
ወላጅ ከልጆቹ፡ ዘመድ ክዘመዱ፡ የሚተያይና የሚጠያየቀው?

በነጻ ተንቀሳቅሶ፡ ተምሮና፡ ሰርቶ ለመኖር፡ መብት የሚያገኘው፡
እስከ ማእዜኑ፡ እንዲህ ተጨቁኖ፡ በርሃብ ማቅቆ፡ እንዲህ የሚኖረው?

የዚህ እልቂት፡ ውድመት፡ ጠንሳሽና አመንጭዎች፡
የእቅዱ፡ ደራሲያን፡ ተዋኒያንና የተውኔት መሪዎች፡
የነሱ ግብር አበር፡ ስራ አስፈጻሚና አስተባባሪዎች፡

ምን ዓይነት፡ ፍጡር ናቸው ፡ ከምን የመነጩ ከየት የበቀሉ፡
በምን ተመዝነው፡ በምንስ ይለኩ በምን ይመሰሉ፡

ካላንዳች ርህራሄ ህዝብን፡ የጨረሱ ሰውን የገደሉ፡
ካህናት መነኮሳት አዛውንት ሳይሉ፡
ሰው ገደል የጣሉ፡ በእሳት ያቃጠሉ።

በፍፁም ጭካኔ፡ ህፃናት፡ ያረዱ፡ ሴቶች የደፈሩ፡
ታድያ! እነዚህ አህዛብ፡ ምን እንበላቻው፡ በምን ስም ይጠሩ?

በምን ይመሰሉ፡ ምን ቅፅል እንስጣቸው፡
ላደረጉት ድርጊት፡ ለፈፀሙት ጸያፍ፡ የሚመጥናቸው?
ሰው እንዳይባሉም፡ ስብእና የላቸው፡
ሰይጣን እንዳይባሉም ከሱ፡ የባሱ ናቸው።

ድርጊታቸው መጥፎ፡ ምግባራቸው እኩይ፡
ስራቸው አስጸያፊ፡ ተልእኮቸው እቡይ፡፡

ጭካኔአቸው ልክ አልባ፡ ክመጠን ያለፈ፡
ወንጀላቸው፡ ግዙፍ፡ የተትረፈረፈ።

ሰይጣንን፡ የሚያስንቅ፡ መስተጋብራቸው፡
አውሬንን የሚያስንቅ፡ ዘግናኝ ጭካኒያቸው፡
ሰው ያልሆኑት፡ ሰዎች ማን እንበላቸው?

ማይካድራ ላይ ያሳዩት፡ በጅምላ ሰው መግደል፡
ባኩስም የፈፀሙት፡ የዘር ማጥፋት ወንጀል።
ትግራይ ውስጥ ያስኬዱት የሰው ልጅ ጭፍጨፋ፡
የሴቶችን፡ መድፈር፡ የሃብት ምዝበራ፡ የንብረት ዘረፋ፡
የህፃናት ቅትለት፡ ያዛውንት እንግልት፡ የመብት ገፈፋ፡፡

የታየው ጭካኔ፡ የተፈጸመው ግፍ፡ ፍዳና መከራ፡
ለማመን ሚያዳግት፡ ከመጠን ያለፈ፡ እጅግ ነውራም ስራ።
የሰውን ልጅ ሬሳ፡ ሜዳ ላይ የጣሉ፡ ገደል የከተቱ፡
ቁም ስቅል ያሳዩ፡ ሴት ወንዱ፡ ህፃን አዛውንቱ።
ታድያ! የዚህ እኩይ ተግባር፡ ፈፃሚ/አስፈፃሚ፡ የሆኑትን ሁሉ፡
በምን መመዘኛ፡ በየትኛው መስፈርት፡ ሰዎች ይባላሉ?

ደቂቀ ሳጥናኤል፡ የዲያብሎስ ምእመናን፡
ያጋንኔን ደቀመዝሙር፡ የክፋት መምህራን።

የቂም በቀል ምንጮች፡ የጥፋት ጎተራ፡
ምግባራቸው ከይሲ፡ ፍሬያቸው መራራ፡
ፍፁም አረመኔ፡ ጨካኝ ደሞተራ፡

ክህደት እንደ ይሁዳ፡ እርኩስ፡ እንደ በላኤ ነብስ፡
ጨካኝ እንደ ሄሮድ፡ ውጉዝ ከመ አርዮስ።

ሀብትና ንብረቱን፡ ቅራቅምቦው ሳይቀር፡ ጠራርገው የሄዱት፡
ቤቱን አቃጥለው፡ ንብረቱን አውድመው፡ ባዶጁን ያስቀሩት።

በቂም፡ በጥላቻ ታውረው፡ ለሰይጣን ያደሩ፡
ህሊና አልባ ኩፍዎች፡ ለሰው የማይራሩ
በቂም ተኮትኩተው፡ በበቀል የለሙ፡ ያፈሩ፡
ለጥፋት ተሰርተው በቅለው ያጎመሩ፡
ደቂቀ አጋንንት፡ እጉዋለ ሳጥናኤል፡ አበአርዮስ ነበሩ።

በትእቢት ተምረው፡ በክፋት ደቁነው፡ በነውር፡ የቀሰሱ፡
በተንኮል ተክነው፡ በጥላቻ ከብረው፡ በቂም የጰጰሱ፡
በርክሰት ተወልደው፡ በማጭበርበር አድገው ፡ባሰት የነገሱ፡
ካላንዳች ሃፍረት፡ ቀሳውስት የገፉ፡ መስጊድ የደፈሩ፡ እምነት ያረከሱ፡
ንዋየ ቅዱሳትን ዘርፈው/ያዘረፉ፡ ጽላት የሰረቁ፡ መቅደስ ያፈረሱ።

ቀሳውስት፡ መነኮሳት፡ አዛውንት፡ መበለት ፡ ባልቴትን ሳይሉ፡
ህሙማን፡ ደካሞች፡ ሕጻንት፡ ታማሚው፡ አካለ ስንኩሉ፡
ሁሉንም ያንገላቱ፡ ያዋረዱ ፡ ያዋከቡ ያጉላሉ።

ፍየልና በጉ፡ የቀንድ እና የጋማ ከፍት፡
ሴት፡ ወንድ፡ ልጅ፡ አዋቂ፡ ድሃ፡ ባለንብረት፡
ማን ከማን ሳይለዩ፡ ፍጡራን የሆኑትን ሁሉ፡
በማንነት መስፈርት፡ ህዝብን ገደለው፡ ያስገደሉ፡፡

በግፍ ፡በጭካኔ፡ ሀብትን ያወደሙ፡ ማንኪያ ሹካ ሳይቀር፡ ንብረት የዘረፉ፡
አገርን እንደአገር ፡ህዝብን፡ እንደህዝብ፡ ሊያመክኑ ሊያጠፉ፡

በውል፡ መክረው ዘክረው፡ አቅደው ፡ ለጥፋት ያበሩ
ትግራይን እንዳገር፡ ትግራዋይን፡ እንደ ህዝብ፡ ሊያጠፉ የሞከሩ፡
በሰፈሩት ቁና፡ ተሰፍረው፡ በቆፈሩት ጉድጉዋድ፡ ገብተው ተቀበሩ።

አንዱ፡ ካንዱ አይሻል፡ ካህን ከዲያቆኑ፡ ቀሲስ ከመነኩሴው፡ጳጳስ ከምእመኑ፡
ስቪል ከወታደር፡ ገጠር፡ ከከተሜው ምሁር፡ ክማይምኑ፡፡

ሊቁ ከደቂቁ፡ ተራው ህዝብ፡ ሊህቁ፡ አጥፊ የሆነበት፡
ውድመቱን፡ ጥፋቱን፡ ቅትልቱን፡ የሚያወግዝ መካሪ የጠፋበት፡
መጥፎ ዘመን ነበር፤ ቀውጢ ጊዜ ነበር፡ የተዛዘብንበት።

አብየት ትበል ትግራይ፡ የተደፈረችው ፡የተወረረችው፡
እርይ ትበል አክሱም፡ ልጆቹን ያጣችው፡
ነጋሺ፡ ክስ ታቅርብ፡ የተደበደበች፡ የተቃጠለችው፡
ማይካድራ ትናገር፡ ባልሰራችው ወንጀል፡ ፍዳዋን ያየችው፡
እልል ትበል ተምብየን፡ ዘግየት፡ ብላም ቢሆን፡ ድል ያበሰረችው።

በማህበረ ዴጎ፡ ዳሞና ዋልድባ፡ በሌሎችም አድባራት፡
የጠፉት አልባሳት፡ መፃህፍት፡ ንዋየ ቅዱሳት፡

የመሰቦ ስሚንቶ፡ ያልመዳው፡ ጨርቃጨርቅ፡
የመስፍን እንዱስትሪ፡ የሰለኽለኻው ወርቅ፡

ያዲግራት ፋርማሲ የሕሞራው እርሻ፡
የተከዜው ግድብ፡ የተምብየኑ ዋሻ፡

የአሽጎዳው ነፋስ ሀይል፡ የራያውን ቢራ፡
የግባው ወንዝ ልማት፡ ውሃ ግድብ ስራ፡

አረ አሉ ሌሎችም፡ አሁን ያልተወሱ፡ በየልማት ዘርፉ፡ በየእድገት አውታሩ፡
በማን አለብኝነት፡ የተሰረቁና የተበዘበዙ፡ የተዘረፉና የተመዘበሩ።

ተጋብቶ፡ ተዋልዶ፤ አብሮ በልቶ ጠጥቶ፡ ባንድነት የኖረ፡
ባንድ አገር፡ ባንድ መንግስት፡ በወል ስም ሲጠራ የነበረ፡

ክፉንና ደጉን፡ መከራና ደስታን አብሮ የተቀበለው፡ አብሮ ያሳለፈው፡
አብሮ የተዋጋ፡ አብሮ የተዋደቀ፡ ለእድገት፡ ለልማት አብሮ የተሰለፈው
ምነው፡ ምን ተገኘቶ፡ እንዲህ አውሬ የሆነው፡ ወገን በወገኑ እንዲህ የጨከነው፡
ህዝብን እንደ ህዝብ፡ አገርን እንዳገር ፡ለማጥፋት፡ ከሌላ የወገነው?

በተለይም ያኛው! የትግራይ ህዝብ፡ ጎረቤት የሆነው፡
እምነቱን፡ ቅዋንቃውን፡ ወጉን እና ባህሉን፡ የሚጋራው፡፡

በዛ በክፉ ቀን፡ የትግራይ ህዝብ ልጆች፡ ውለታ የዋሉለት፡
ነጻነቱን እንዲያገኝ፡ የተከራከሩ፡ ጥብቅና የቁሙለት፡
በየአደባባዩ፡ የተምዋገቱለት፡ በየጦር ግንባሩ የተዋደቁለት፡
በዚህ መልክ ነበር ውለታው፤ ብድሩ፡ መከፈል፡ ያለበት?

እኒህ ነውረኞች ግን፡ ያደረሱት በደል የፈጸሙትን ግፍ፡
ፍጹም ዘግናኝ ነበር፡ ለማየት የሚከብድ፡ ለመስማት የሚቀፍ።

ጎተራው አፍርሰው፡ ቡቃያውን አውድመው ፡አቃጠሉት ምርቱን፡
ጋማ ከብቱን ዘርፈው፡ ቀንድ ከብቱን በልተው፡ ተሸክመው ሄዱ፡ ቡሀቃው ዱቄቱን
ሀብቱንም መዘበሩት፡ ቤቱን አቃጥለው፡ ደፈሩበት ሚስቱን፡

ልጆቹን ገደሉ፡ ንብረቱን ዘረፉ፡ ሞፈር ቀንበር ሰብረው፡ በሮቹን አረዱ፡
ባዶ ቤት አስቀሩት፡ እርቃኑን አቆሙት፡ በግና ፍየሉ፡ ከብቶቹንም ነዱ።

የበደሉት በደል፡ የፈጸሙት፡ ድርጊት፡ ያሳዩት መጨከን
አጀብ ነው! የሚይስብል ነው፡ እጅን ባፍ የሚያስጭን።

ለነሱ ይብላኝ እንጂ፡ እንዲህ ለቀለሉትና እንዲህ ለዘቀጡት፡
ቡክርናቸውን ለሽጡ፡ ለተዋረዱና ሰብእናቸው ላጡት።

ትግራይስ፡ ታድጋለች፡ ትመነደጋለች፡ በልጆችዋ ብርታት፡ ድል ትቀዳጃለች፡
በጠላት መቃብር ላይ፡ ጎልታ፡ትታያለች፡ የህዳሴዋም ድል፡ ላለም ታበስራለች።

ዛሬም አልዋት ልጆች ድሮውም ነበርዋት፡
ክብርዋን አስጠብቀው እስካሁን ያቆያውት፡
መሪዎችም አልዋት እንዲሁም ነበርዋት፡
እንደዘመኑ ባህል የመርዋት፡ የተዋደቁላት።

ላብነትም ያህል፡ ጥቂቶችን እናንሳ በውል ከታወቁት፡
ደግዋለ ተዋግተው፡ ጠላት ድል የነሱት፡
ዓድዋ ላይ፡ ተፋልመው፡ መተማ የወደቁት፡
ክዋአቲት ጦር ገጥመው፡ ሊማሊሞ ያለቁት፡
በማይጨው ጦር ሜዳ፡ መስዋእት የሆኑት፡
በአላጌው ውጊያ ወቅት፡ ጀብዱ የፈጸሙት።

በደም ባጥንታቸው፡ ድንበር የጠበቁ አገር ያስከበሩ፡
ወቅቱ በሚፈቅደው፡ አገርን የመሩ፡ ህግን ያስከበሩ፡
ባንፀባራቂ ድል፡ ክብር፡ የተጎናፀፉ፡
በወርቃማ ቀለም ስማቸውን ያስጻፉ፡፡

እንደነ መንገሻ፡ አባ ግጠም፡ አባ በዝብዝ ካሳ፡
አብርሃ፡ አባ ዝናብ፡ አባ ይባስ ጉግሳ፡
አባ ክበድ ገብሩ፡ አባ ይላቅ ካሳ፡
መሸሻ፡ አባ ደምሥ፡ አባ ግዛው ማሩ
አባ በርዝ ስዩም፡ አባ ቅጣው ገብሩ፡
ገብርሄት፡ አባ ፈንቅል፡ አሉላ አባ ነጋ፡
አባ ቀማው ጉዋንጉል፡ ስዩም አባ ይርጋ።

ሌሎችም ነበርዋት፡ ትውስትና ዝክር፡ ስብሃት ሚገባቸው፡
በክብር የወደቁ ላገር፡ ለህዝባቸው።

ለወገን ክብር ሲሉ፡ መስዋእት የሆኑት፡
እንደነ ሐየሎም፡ አግዓዚ፡ ዋልታና ቀለበት፡

እንደነ አሞራና ስሑል፡ ሙሴና፡ ቀሺ ገብሩ፡
ውድ ሂወታቸውን፡ ለህዝብ የሰጡ፡ ላገር የገበሩ፡

እንደነ አባይ ጸሐየ፡ ስዩም፡ ሴኩትረ፡
እንደነ ገዛኢ፡ ክዋርተርና አስመላሽ፡ ሰዓረ፡
ዝንታለም፡ ይኖራል ዝናና ስማቸው፡ እንደተከበረ።

መዘገብ፡ ያለበት፡ ሌላም ታሪክ አለ፡ ሁሉን ያካታተ፡
የትግራዩን ወጣት፡ የቲዲኤፍ አባል በተመለከተ፡
የዓላማው፡ ፍትሀዊ መሆን፡ የህዝብ አንድነቱ፡
ያለምን፡ ቀልብ የሳበ፡ ይዘቱ፡ ቀመሩ፡ ትርክቱ።

ድሉ ቀናኝ ብሎ፡ ሲፎክር፡ ሲሸልል፡ ጠላት ሲደነፋ፡
ጁንታው ጠፋ፡ ብሎ ነጋሪት ሲደልቅ፡ መለከት ሲነፋ፡

ጥላቻ ሲሰብኩ፡ ጥፋት ሲያስተምሩ፡ ክፋት ሲለፍፉ፡
ለከት ያጣ ውሸት ሲረጩ፡ ሲዘሩ፡ ሲያስፋፉ፡
በድል ወጣን ብለው፡ እነ ባጫ፡ ጁላ፡ ጥሩምባ ሲነፉ።

ትህነግ፡ ዱቄት ሆነች፡ እያሉ ሲያወሩ ሲያስወሩ፡
ጠላትን ድባቅ መትተን፡ ድልበድል ሆነናል፡ እያሉ ሲኩራሩ፡

እነ ዳነኤል፡ መሽረፈት፡ ድቤያቸው ሲመቱ፡ ሲነፉ ቱልቱላ፡
እነ እምሬት፡ እነ ኢራን፡ እነ ቱርክ፡ ሲያቀብሉ ዱላ።

አፈር ልሶ፡ እሳት ጎርሶ፡ ሲነሳ፡ ባላሰቡት ጊዜ፡ ባልጠበቁት ቦታ፡
ድንገት፡ ብቅ ብሎ፡ ያዋክባቸው ጀመር፡ ይነሳቸው ፋታ፡

በራሳቸው ነዳጅ፡ በራሳቸው ክላሽ፡ በራሳቸው ድሽቃ፡
በራሳቸው መድፍ፡ በራሳቸው ታንክ፡ መሳሪያና እቃ፡

በቆረጣ ገብቶ ጠላትን ድል መታ፡ ከነ ተላላኪው ከነ ግብራበሩ፡
ከነረዳቶቹ፡ ከነአይዞህ ባዮቹ፡ አሰልጣኝ፡ መምህሩ።

በሳምረው ጦርነት፡ በግጀቱ ውጊያ፡
በፊናርዋው ግጭት ባበርገሌው ፍልሚያ፡
በአግበው ከበባ፡ በወርሰገው ግጥሚያ፡
በየጭላው ትንቅንቅ፡ የጨበጣ ውጊያ።

በእዳጋ አርቢው፡ ውጣውረድ፡ በወርቃምባው ውሎ፡
ምድር ቀውጢ ስትሆን፡ ውጊያው ተጋግሎ፡
ጠላት ሲሸሽ ፡ ሲፈረጥጥ ፡ መሳሪያውን ጥሎ

የጠላት ጦር፡ ድል ተመታ፡ ተወቃ፡ ታሸ፡ ተበተነ፡
ድምጥማጡ ጠፋ፡ የ ዶግ አመድ ሆነ፡
ባጋጠመው ሽንፈት፡ አፈረ ፡ እጅግ ተዋረደ፡
ዳግም ላይመልስ፡ እንደ ጢስ በነነ፡ እንደ ጭድ ነደደ።

እግሬ አውጪኝ ብሎ፡ ጠላት ግራ ገብቶት፡ ሲሮጥ ሲፈረጥጥ፡
ተከታትሎ ወቃው፡ ድንበር ሳይሻገር፡ ሳይሸሽ፡ ሳያመልጥ።

ኮረም ላይ ድል መትቶ፡ ግራካሕሱ ገባ፡ የ ቲ.ዲ.ኤፉ ጦር፡
አላማጣ፡ ቆቦ፡ ወልድያንም አልፎ፡ ደሴን ሊቆጣጠር፡

ጋሸናን አቅዋርጦ፡ መርሳን ተሻግሮ፡ ኮምበልቻን ሊከልል፡
ካራቆሬን አልፎ፡ ደብረ ብርሃን ዘልቆ ፊንፊነን፡ ሲከጅል።

ተዋግተው፡ እያዋጉ፡ ይህን ጦር እየመሩ፡ ታእምርን የሰሩ፡
ያሳዩት ጀግንነት፡ የፈጸሙት፡ ጀብዱ፡ ድሉን ያበሰሩ፤
አንክዋር አንክዋሮቹ እነዚህ ነበሩ።

ያሳዩቱን ክህሎት ቢቀመር፡ ቢተመን ቢሰላ፡
የጦር አበጋዙ፡ ታደሰ ወረደ፡ ጻድቃን አባመላ፡
ደፋሩ፡ ወድ እምበይተይ፡ ትንታጉ፡ ወድ አሸብር፡
መዲድ፡ አባ ውቃው፡ ድንኩል አባ ስበር፡

ገብሬ፡ አፈ ጦሩ፡ ምግበይ አባ መብረቅ፡
በቆረጣ፡ ገብቶ ጠላትን ሚያስጨንቅ፡

መራሄ መንግስቱ፡ ደብረጼዮን መሪያቸው፡
ሁለገቡ፡ ታጋይ፡ ዘጋቢው ጌታቸው፡
ሁሉም በጥቅሉ፤ “ያኢስ”! ይበል! የሚባሉ ናቸው።

ሌሎቹም አባላት፡ በየቦታው ያሉት፡ በየጦር ግንባሩ፡
በየልማት መስኩ፡ በየስራ ዘርፉ፡ በማስተዳደሩ፡
በየፖለቲካው፡ ዲፕሎማሲ ስራ፡ እንደ ሻማ ነደው፡ ለሰው የሚያበሩ፡
ሁሉም እንዲሳካ፡ ግቡን እንዲመታ፡ የወጡ የወረዱ፡ ሌት ተቀን የሰሩ፡
ደከመን፡ ተቸገርን ሳይሉ፡ ዳገቱን የወጡ፡ ሜዳው ያማተሩ፡
ወጣት ሽማግሌው፡ ሴት ወንዱ፡ ማህይምን ምሁሩ።

ሁሉም በየፊናው፡ አቅሙ በፈቀደው፡ በሚችለው ሁሉ፡
ነጋዴ፡ ገበሬው፡ ባላገር ከተሜ፡ ሀብታም ባለንብረት፡ ድሀ ሳይባሉ፡
ሁሉም ተዋድቀዋል፡ ሁሉም ወጥትዋል ፡ ወርድዋል፡ ላገር ክብር ሲሉ።

ህዝብን የጠበቁ፡ አገር ያስከበሩ፡ የከፈሉት፡ ውድ ሂወት፡
ምሉእ በኩለሄ፡ እንከን የሌላቸው ፡ በምግባር ፡በክህሎት
ይደልዎም ክብር! ይደልዎም ሞገስ! ይደልዎም ስብሃት።

ደስ ይበላት ትግራይ! ትፈንድቅ! ትኮፈስ! በልጆችዋ ትኩራ!
በከፈሉት መስዋእት፡ ባሳዩት ጀግንነት፡ በፈጸሙት ስራ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *