የትግራይ ሕዝብን ክህደት እስከመቼ?

News

ሚኒሊክ አገዛዝ ጀመሮ፤ ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ ብለን ትላልቅ ሰይጣኖች አጠገባችን አስቀምጠን ሕዝባችንን ባለማንቃትና ባለማስታጠቅ፤ ብዙ ዋጋ እንድንከፍል ተገደናል። ከአሁን በኃላስ አያያዛችንና አኗኗራችን እንዴት ሊሆን ይችላል? በጥልቅ ሊታሰብበትና ሊገመገም የሚገባው ሁኔታ ላይም ደርሰናል። ሕልውናችን ከምን ጊዜው በላይ ፈተና ውስጥ ገብቶ የተያበት ጊዜ ቢኖር፤ በአሁን ሰዓት ላይ የደረሰብን የ፫፻፷ (360)ዲግሪ ከበባ ውስጥ መግባታችን ነው። ፖለቲካ ሽፍጥ፤ ሃይማኖት ሃጥያት በሆነባት ኢትዮጵያው ውስጥ ሆኖ መኖር እንደማይቻል፤ በሕዝባችን ላይ የደረሰው ግፍ አይነተኛ ምስክር ነው።
የደረስብንን በደልና ጭካኔ ቢጻፍ የታሪክ መዝገብም የሚበቃው አይመስለኝም። ከኢንደስትሪ አብዮት ይልቅ ያልዋለበትን የጦር አውድማን እንደ ጀብድ የሚያወራ በተዘከዘከበት ማህበረሰብ ውስጥ ተካተን፤ የትግራይ አልገዛምነትን ታሪክና ገድል ተሰርቆብን፤ አቤት ሳንል አብረን እንደመዥገር ተጣብቀውብን ደማችንን ሲመጡ ከነበሩት ጋር ታሪክ መጋራቱ፤ አይነተኛው ስሕተታችን ይመስለኛል። ይሄን ሁሉ ጥፋት እስከመቼ ድረስ ሳንቃችን ላይ ተሸክመን ሕዝባችንን እያስፈጀንስ እንኖራለን? አቢሲኒያን ተብለን ታሪካችንን ጠብቀን በነበረበት ወቅት፤ የስልጣን ጉልበቱ በመሃል አገር ሽፍጥ ወደ ሸዋ ሲዘልቅ ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ተሰጠን። የታሪክ ቅርሶቻችና ገድሎቻችን የሚያንፀባርቁ የከበሩ ድንጋዮቻችን፤ በመጡ የመሃል አገር ገዢዎችና ከውጭ በመጡ ወራሪዎች በባንዳዎች ታግዘው አንዲወድሙ አንዲጠፉና እንዲሰረቁ ሲደረግ፤ ዘመናትን አስቆጥረን ኢትዮጵያዊ ተብለን ኖረናል።
አሁን የተቃጣብን ዘመቻ ከምን ጊዜውም በላይ ለየት የሚያደርገው ፫ አይነታዊ ገጽታዎችን ከዚህ በታች እንደሚከተለው አስቀምጣቸዋለሁ።
፩) በሕወሃት የሚመራው የኢሕአዴጉ መንግስት ደርግን ከገረሰሰ በኃላ ሰለ ኢትዮጵያ ተብሎ ታጥቆት የመጣውን መሳሪያና የሰው ሃይል በሕገመንግስታዊ ሽፋን ላዋቀረው የፌደራል መንግስት አስረክቦ፤ ፊቱን ወደ ልማት አዞረ ወረቀት ላይ የተጻፈው ሕገ መንግስት ያድነኛል በሚል ተስፋ። አይ ተስፋ፤ ቃሉ እንዴት ደስ ይላል የታሰበው ቢፈጸም ኖሮ።

፪)ትግራይን ለማጥፋት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከተሳተፉት አገራት ዉስጥ አይነተኛ አስተዋጽኦ ያረጉት፤ አረብ ኢመሬት፣ ቱርክ፣ ኢራን፤ ሳኡዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ፓኪስታን፣ ሶማሊያ ሪፐብሊክ፣ ኤሪትሪያ፣ ቻይና፣ ራሺያ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ታሪካዊ የትግራይ (አቢሲኒያ) ጠላቶች ናቸው። ከ፲ (10) አገራት ፯ (7)ቱ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለኢትዮጵያ ጥሩ የሆነ አመለካከት ያላቸው አይደሉም አልነበሩምም ከአሁን በኃላም ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምትም የለኝም።
፫)ኤርታራ ስለዚች ባሕረ ነጋሽ ተብላ ትጠራ የነበረች አገር የቱ ጋር ልጀምር እንደምችል ባላውቅም፤ አንድ ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው ነገር ግን አለ። ኢሳያስ የሚባል በተግባሩ ሰይጣን የሚቀናበትን ሰው፤ ጎረቤት አርገን እየኖርን አይነታዊ ለውጥ አምጥተናል ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩነት ቢኖረንም ስራችን ያወጣናል እንጂ የከፋ ነገር አይደርስም ተብሎ የዋህነታችን ማንነታችንን ከምንም ጊዜውም በላይ እንድነጠቃ አረገን።
ከለፈው ፪ ዓመት ሳይሆንጦርነት የታወጀብን ኢሳት የሚባለው የዜና ማሰራጫ ከተቛቛመ ከዛሬ ፩፬ (14)ዓመት በፊት ጀምሮ ዘር ተኮር (ትግራዋይን) ለይቶ ለማጥቃትና የኢትዮጵያን ሕዝብ በመንጋ አንድ አይነት የጥላቻ አስተሳሰብ ትግራዋይ ላይ እንዲኖረው በማድረግ ይህ ነው የማይባልና የማይነዛ ፕሮፓጋንዳ አልነበረም። ሕዝቡም ይሄን ሰምቶ በሕዝባችን ላይ ይህ ነው የማይባል በደል ሲፈጸም እያየ ዝም እንዲልና፤ ከማንኛውም የማህበረሰብ ድርጅት አንስቶ እስከ ሃይማኖት ተቛማት ድረስ፤ ትግራዋ ላይ የታወጀውን የጅምላ ጭፍጨፋ እጃቸውን ደረታቸው ላይ አድርገው ሲደግፉ የታዩት። ከምንም በላይ እነሱ ከሚገዙን ሰይጣን ቢገዛን ይሻላል ብለው ቀሳውስቱ የተናገሩት ጸያፍ ቃል ከእያንዳችን አእምሮ የማይጠፋ፤ ለዘላለሙ የማይሽር ጠባሳ ጥለውብን ነው የሄዱት።
አሁን ለደረሰብን የእልቂት ዘመቻም ግብጽና ኤርትራ በመተባበር የዚሁ ዜና ማሰራጫ አጋር በመሆን የዘር ማጥፋት ዘመቻው እንዲቀጥል በማድረግ ለ፲ ዓመት ያህል ዘልቆ ለዚህ በቅተናል።
ከላይ የጠቀኳቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ይሁኑና እንዴት የትግራይ የፖለቲካ የበላይነት ከአፄ ዮሐንስ ሕልፈተ ሕይወት በኃላ ወደ መሃል አገር ሄደ??

የመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉ ሕዝባችንን ሊጨፈጨፍ ቻለ??
በተለይ ጣልያንን አድዋ ላይ፤ ራስ አሉላ አባ ነጋ ድል ካደረጉት በኃላ የፕሮፓጋዳውን ስራ ባለመስራታችን ይሁን ወይም ሞያ በልብ ነው ብለን ታሪካችንን ገድሉ ላይ ላልዋሉበት የታሪ ፀሃፊዎች ሰጥተን እንዲህ ተጣሞና ተንጋድዶ አንዲጻፍ ያበቃነው። እስከር ቅርብ ጊዜም ድረስም የሚኒሊክ ገድል ተደርጎ ሲተረክ የነበረው። ሀይለ ስላሴም ቢሆን የቀዳማይ ወያኔን ትግል የትግራዋይነት አልገዛም ማለትን ለማክሸፍ፤ የእንግሊዝን መንግስት በመለምን ከየመን የተነሱ አይሮፕላኖች በመቀሌ ላይ የቦምብ ጥቃት በማስድረስ ሕዝባችን ላይ የእልቂት ዝናባቸውን ያወረዱብን። የዚህም እልቂት በአግባቡ ሕዝባችንን ለማንቃት የተጠቀምንበት አይመስለኝም። ምክኒያቱም ሕዝባችን ወደሚቀጥለው የትጥቅ ትግል ለመግባት የወሰደበት ጊዜን ሳስብ አሁንም የቤት ስራችንን በአግባቡ ተወጥተናል ለማለት ይከብደኛል።
የአልገዛም ባይነቱም በ፷ዎቹም (በ60ዎቹ) ዓመት ላይ እንደገና ተቀጣጥሎ በመነሳት በ፹ዎቹ (በ80ዎቹ) መጀመሪያ ላይ ሕወሃት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ቀቆጣጥሮ የቢሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት አረጋግጣልሁ በማለት ክልሎችን አግዝፎ በመፍጠር ትግራይ አሁን ላለችበት የጥፋት አደጋ አሳልፈው ሰጧት። የአሁን በደል የከፋ የሚያረገው፤ ሕወሃት ያሳደገቻቸው ከሃዲዎች የአያቶቻቸውን ምኞት እያስቀጠሉ ያሉት ከባእድ አራዊት ሰራዊትና ከታሪካዊ የአቢሲኒያ (ትግራይ) ጠላቶች ጋር በመተባበር መሆኑ ነው። ከበባውንም ሰብረን ወጥተን ደብረ ብርሃን በደረስንበት ወቅት ሕዝባች የተጠማውን ሰላም ለማግኘት ተቃርቧል በምንልበት ሰዓት ለሰላም እድል እንስጥ በሚል ምክኒያት ( ሰራዊቱን ወደ ነበረበት ቦታ በመመለስ ሌላው የየዋህነት ውጤት ስሕተት እንደገና ተደገመ። (እዚህ ላይ ሚስጥራዊ የሆነ ተግባር የተፈጸመ ሆኖ ይሰማኛል ወደ ኃላ ማፈግፈጋችን)::
እስከመቼ ዋጋ ከፍለን ያመጣነውን ድሎች አሳልፈን በመስጠት ሕዝባችንን ለጥፋትና አደጋ እንዳርገዋለን??
ይሄን ጽሁፍ ሳዘጋጅ ከላይ የጠቀስኳቸውን ስህተቶች እንድንማርባቸው፤ ለቀያጣዮ መፃኢ ማንነታችን ስር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት እንዲያስችለንና ዳግም ከዚህ ቀደም የተሰሩትን ስህተቶች እንዳንደግማቸው፤ ልጆቻችንም

እንዲማሩበትና ማንነታቸው አውቀው እንዲያድጉ እንጂ፤ ጣት እየጠነቆልኩ በስልጣኑ ላይ የነበሩትንና ያሉትን ሰዎችን ለመኮነንና ሃጥያታቸውን ለማብዛት ብሎም በመካከላችን ላይ ልዩነት ለመፍጠር እንዳልሆነ ከወዲሁ ይታወቅ ዘንድ በኣክብሮት ኣሳስባሎሁ::

ሉሉ መከነን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *