ምን፣ ምን…ኣልክ! ምኒልክ?

News

Please click here to watch the AI video of Minilik’s message.


ምን፣ ምን…ኣልክ! ምኒልክ?

ምንሊክ ምን እይነት ሲራራ ነጋዴ
ሱቅ ከፍቶ እንደመሸጥ ስንዴ
ወይም ጨርቃ ጨርቅ ነጠላ
ወይም ብልጭልጭ ቅይጥ
ሲሯራጥ ከረመ ቁርጥርጥ
ኣድርጎ ሃገርን ለመሸጥ::

በሱ ኣያልቅ
ጥፋቱን ሳያውቅ
ሃፍረት ሳይደባልቅ
ዓይነ ደረቅ
እንደመፀፀት ይቅርታ መጠየቅ
ከሸጠ በኃላ ገንዘብን ቆርጥሞ
ኣደባባይ ቁሞ
የሸጠውን መሬት
ላንቶንዮ ሮቤርቶ
የኔው ነው፣ የራሴ ድህረቤት
ካለ ውሃ ምጠጣበት
መርከብ እምጔዝበት
ኣሣ ማጠምድበት
ምን ይደርግልኞል ይህ ደረቅ መሬት:
መልሱልኝ አልዝያ በጉልበት
ላንቶንዮ ኣስክሪስ/Askaris ለማበሳጨት:

ለኔ ለኔ ሲሉ
ሁለት ወሮበሎች ቢታገሉ
ቢቓስሰሉ ቢጋደሉ
ማን ሞኝ ይገባል በማሃሉ:
ድሮ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
ኣሁን ምን ያደርጋል
ከወደቁ ማልቀስ::

ተመስገን ኸበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *