ኣብይ የዓለም ማራቶን ዋንጫ!
ያለፈው ጣጣ
ግልብጥብጡ ወጣ
የምስራች ብልጽግና መጣ:
ላመታት መሮጥ ኣቅቶን ቆምታ፣
ፈገ ግታ፣ እስክስታ፣
ዶህነት በውን ተረታ፣
ዐብይ ችግራችን ፈታ።
ምን ያለ ደፋር ዓይን ኣውጣ
በእጅ መዳፍ ብቻ ፈጣን ሩጫ
እንድህ ያለ ብልጫ
አሸነፈ ዐብይ የዓለም ማራቶን ዋንጫ።
ይህ ታኣምር ላይበቃ
ሌላኛው የሴቶች ቡድን ኣለቃ
የኋላኋሊት ስትሮጥ
ድህረ ጀርባዋ ቦሪጥ
ሲል ገልበጥ ፈጠጥ ገልበጥ
ሲወረወር እንደ ጭፊት
ሲያዩት ሚያስደነግጥ
ተፎካካሪ ሮዋጭ ዓይን አደንዝዞ
ወደኌላ ሚጎትት።
በዚህ በል በዛም፣ በቃ
ሬኮርድን ሰበረች ጨፍልቃ
ዝናን ኣዳነች ጠንቅቃ ።
ታኣምር ነው ማራቶን የዘንድሮ
ኣዲስ ሜላ ቦርብሮ
የወዱ በል የሴትየዋ ንሮ
መንዝሮ መነዛ ዝሮ
ኣወጣው ከደሳሳ ጔሮ
ብልጽግናን አነገሠ እየገሠገሠ ለደሄየው ወገን ቤቱ ለፈረሠ
ሃለሉያ፣ እሰይ እሰይ ኣዳነች ዝናሽ ተቀደሠ።
ተመስገን ከበደ