የነውጥ ስርዓት በኢትዮጵያ።
በተላላኪዎች ለምትተራመሰው ኢትዮጵያ የተላላኪዎችን ገጸባሕሪ የሚገልጽ ተግባር።
በአለማችን ብዙውን ጊዜ የሕዝብ አመጽና የመንግስት ለውጥ የሚታየው የኢኮኖሚ እድገት ባለመኖሩና የስራ አጥ ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ነው። ኢትዮጵያ ላይ የታየው ግን የተገላቢጦሽ አይነት ክስተት ይመስላል። በሁለት ዲጂት ቁጥር ኢኮኖሚዊው እያደገ በነበረበት ወቅት የሀብት ክፍፍሉ ሚዛናዊ አይደለም በሚል ምክኒያት የሕዝብ አመጽ ተነሳ። በተለይ በአማራና በኦሮሞ ክልል ባደረገው አይነተኛ የሕዝብ አመጽ (ኦሮ አማራ) በሚል ጣምራነት፤ የለውጡ ብቸኛ ባለቤት ሆነው ብቅ አሉ። ኢሀዴግም ራሴን መርምሬአለሁ ብሎ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር መረጠ። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የፖለቲካው ቁማር የተጀመረው። ክሕወሃት መራሹ ኢህአዴግ ወደ ኦሮ አማራ ኢሀዴግ የተቀየረው። ወዲያው ሕወሀትን ለመምታት እንዲያስችላቸውና መንበረ ስላጣኑን ለብቻቸው ለመቆናጠጥ፤ ባለፈው ፪፯ ዓመት እኛ(ኦሮ አማራዎቹ)ኢሕአዴግ፤ የሕወሃት ተላላኪ ነበርን እንጂ ከደሙ ንጹህ ነን ብለው እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ታጠቡ።
ያኔ እነሱ ተላላኪ በነበሩበት ወቅት ኢትዮ ኢኮኖሚዋ እያደገ ሰው በአሻው ስዓት ወጥቶ ወደፈለገበት መንቀሳቀስ ይችል ነበር።
በአሁኑ ወቅት ግን ተላላኪዎቹ የሻእቢያ ጭን ገረድ ሆነው ለሌላ ባእድ መንግስት እየተላላኩ የአገሪቷ ኢኮኖሚ የምግብ ዘይት መግዛት እስኪያቅተው ድረስ ተንኮታክቶ እንዲገኝ አደረጉት። ድፍን መላ አገሪቱ ሰላም በማጣት ወደ እርስ በርስ ጦርነት በማምራት ላይ ትገኛለች፤ የዩጎዝላቭ እጣም እንዳይደርሳት የብዙዎች ስጋት ሆኗል። እዚህ ላይ ሊስተዋል የሚገባው ነገር ቢኖር ስልጣን የያዙት ተላላኪዎች ለማን ተላላኪ ሆነው ኢትዮጳያ ላይ አይነተኛ ለውጥ አምጥተው እንደነበረ ነው።
የሚያሳዝነው እውነታ ግን ተመልሰው የሕወሃት ተላላኪ መሆን ስለማይችሉ ውጥንቅጡ በመቀጠል ላይ ይገኛል። ከተግባራቸውም እንደምንረዳው በአለም ላይ ከባእድ አገር መንግስት ጋር በመወገን የራሳቸውን ሕዝብ ያዘረፉ፣ ሴቶች እህቶቻችንን ያስደፈሩ፣ ኢኮኖሚያዊ አውታሮችን ያስወደሙ ያወደሙ፣ ንጹሃንን ያስገደሉ በትግራዋይ ሕዝብ ላይ ያደረሱት በደል ይህ ነው ተብሎ በማይቆጠርበት ደረጃ ላይ አድርሰውታል እያደረሱበትም ይገኛሉ። እዚህ ላይ የታሪክ ዝርፊያው ተወት ላርገውና ወደ ሃሳቤ ማጠቃለያ ላምራ።
ይሄን ሁሉ ሃጥያት የኢትዮጵያን ታሪክ በጀመረው የትግራይ ሕዝብ ላይ ለማደረስ ለምን አስፈለገ? እንዴትሥ ተብሎ በታሪክ ማህደር ላይ ይመዘገባል? አሁን ያልንበት ዘመን ደብተራ በጻፈው ታሪክ የምንመራ ሕዝቦች አለመሆናችንን አለማወቃቸው ነው። አንድ ነግር ግን ያታየኛል፣ የትግራይ ሕዝብ ከምን ጊዜውም በበለጠ የተሻላ ትግራይንና ትርጋዋይነት ለማነጽ የሚያስችለው ደረጃ ላይ መድረሱ ነው። ይሄን ሁሉ እናም እዚህ ላይ ያልተካተቱ የተሰሩብን ሃጥያቶች ሳስብ የማይሻር ጥቁር አሻራ ትቶ በሚሄደው የተላላኪዎች ዘመን መፈጠራችን በጣም የሚያሳዝን ገጠመኝ መሆኑ ነው።
ስሜ ማነው።