ተፈሪ ፈሪ
ፈሪ እንደ ማለት ተፈሪ
ጀግና ብሎ መጥራት ኣሳፋሪ
እግሬን ኣውጭን ብሎ
ሃገር ጥሎ በራሪ
ህዝቡን ጥሎ
በጋየ እሳት ተንጠልጥሎ
ባያቱ ሰንክ በመጣው ቃጠሎ
ሃገር ሲሸጥ ኣብጠልጥሎ
መቼ ኣሰበው በሩን ሲከፍት
ጣልያን እንደሚገባ ብሎ ሰተት።
ይህ ብሎት ኣልበቃ
መቼም ደላላ ኣይረካ፣ ኣይነቃ
ለጣልያኖች የተሸጠ ሃገር እንደ ዕቃ
ወልቃይት በለው ሑመራ
ኣላማጣ በለው ቆቦ መንደፈራ
ሸጠው ለኣማራ
ልጆቹ ሳይቀር እያስፈራ
እየቸረቸረ በጋብቻ ጥምራ
እንደዋትና ለኪሳራ
ባለርስት መሬት እንዲራራ
ብሎም እንዳይስጋ እንዳይፈራ
ተጠራጥሮ የዙፋን ኣልጋ-ባልጋ እኩይ ሥራ።
የተፈራው መች ቀረ
ዝናብ ሳያዛራ፣
ዳንኬራ በዳንኬራ፣
ለዚህ ሁሉ ጦር መከራ
ዳርጎን ኣለፈ ዘር እስከ ዘር በየተራ።
ከተኛበት ሥፍራ
ሂዱና ቀስቅሱት ቢያወራ
ጠይቁት ጥያቄ መራራ
ምን ለመሆን ነበር ይህ ሁሉ የተሠራ?
መቼም ከወራሪ ደም ሥር
የለም ንሥሃን ሚያበሥር
ካለ ትምክህትና ውሸት መደርደር።
እሱም ሆነ ተከታዮቹ መላ ኣጥ ሲራራ
ድንቁርናን እንዲሥራራ
ድህነት እንዲያፈራ
ኣህዛብ ሲጎትቱ ወደኃላ
እንድፍየል በጭራ፣
እነሆ ተላብስን ቀረን ሥቃይ መከራ።
ጦርነት ማፈናቀል፥ መግደል
የጭቆና ውጤት ማዕበል
ኣስቀድሞ ማጤን
ባዕዳዊ ኣገዘዝን መታገል መሸንገል።
በላይ ኣምበላይ