ትልቁ ባንዳ

Poems

(በጫላ ጉዲና) –

እስቲ ማን አለን ‘ንደምኒልክ ባንዳ
ህልናው አፈንድዶ በባዕድ የሚነዳ
እንደ ቄራ ቅርጫ እየቆራረጠ
የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ የሸጠ።

እስቲ ማን አለን ‘ንደምኒልክ ሞኝ
አገሩን ለባዕድ የሚሸጥ ለቅኝ!
የዓድዋ ጦርነት ጀግና ሰው ተብሎ
ተደፋ ‘ንደ ሬሳ፣ ክብልል ‘ንደ አሎሎ።

ባባታቸው ፈለግ ይኸው ሲከተሉ
ሕዝብን እያስራቡ ብልጽግና ሲሉ
ለባዕድ ዓረቦች ሃገሪቷን ሽጠው
ይፈነጥዛሉ ውስኪውን ጨልጠው!

ከቶ አያበቃም ወይ ይኽ መጨማለቅ
በድሃ መቀለድ ሕዝቡንም መጨፍለቅ
ዕዳ ሳይኖርበት ማንም ሳይለው ግድ
ወትሮ ለኢሳያስ ምንም የሌለው እጁን ሲሰግድ!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *