(በጥዑም መዝገቦ) –
ዐብይ አሕመድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂና አማራ ፅንፎኞች ትግራይ ለማጥፋት አበሩ፣
የዳንኤል ክብረት፣ የተመስገን ጥሩነህና የአገኘሁ ተሻገር መርዛማ ምላሶች አሰማሩ፣
ከባእዳውያን ተባብረው ትግራይ ወረሩ::
ታናሽና ታላቅ ሲገደሉ ሴቶች ሲደፈሩ በአረሜኔ፣
በኢትዮዽያ መከላከያ፣ በአማራና በኤርትርያ አራዊቶች ህዝቤን ሲጨፈጨፍ በጭካኔ ባለ መኖሬ፣
በሩቅ ሁኜ ለህዝቤ ድምፅ እንድሆን ቀና ሌሊት ስጮህ አማርሬ፣
ህዝቤን ጭሆቴ በጭላንጭል ተፋ አገኘ በወሬ፣
አልበገር ብሎ ወደ በረሃ ወርዶ እንዲኖር ተገደደ እንደ አውሬ::
የትግራይ ህዝብ ሀገር ሸያጭ ብለው በውሸት ሲወነጅሉት፣
ትግራይን ለማበርከክ በሦስት ሳምንት፣
በ27 ዓመት በትግሬ የተገነባ የአገር እሴት እደአባቶቻቸው ለመሳርያ ሲለውጡት፣
ድሮኖች ተገዙ ከኢራን፣ ከቱርክና ከእመሬት፣
ንፁህ ህዝብ በጅምላ ገድለው ወደ ገደል ሲወረውሩት፣
ንብረት ሲዘርፍና ሲያወድሙት፣
ሴቶች በጭካኔ ደፍረው ምስማር ሳይቀር በማሕፀናቸው ሲያስገቡት፣
ገበሬ እርሻው እንዳርስ ከለከሉት፣ የእርሻ መሳሪዎቹን ሰበሩት አቃጠሉት፣
የኢትዮዽያ ድንበር እንዳይደፈር ያገለገሉ በእውነት፣
ጁንታ ናችሁ ተብለው ታጎሩ በእስርቤት፣
ተገደሉ በኢሰብአዊ ድርጊት፣
ዲያስፖራው ጀኖሳዱን ለዓለም ስያመለክት በጩኸት፣
የትግራይ ህዝብ ወደ ደባይ ውግያው ገባ መረር ባለ ስልት::
የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ጀግንነት በጉያ ቴምብዬን አሰላስሎ፣
የአሉላ ስልት በትግራይ ጀግኖች በእቅድ ተስሎ፣
ጀግናው ት.ዲ.ኤፍ (TDF) ህዝቡን እንድያድን ለዘመቻ ተረባረበ፣
ከቴምቤን እስከ አላማጣ፣ ከሽሬ እስከ ዓዲግራት የወያኔነት መብረቅ አንበለበለ፣
የአረሜኔዎች ሰራዊት በት.ዲ.ኤፍ (TDF) በትር ተለበለበ::
በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ሰይጣናዊ ግፍ በትግራይ ላይ ሲያወርዱ፣
የትግራይ ህዝብ አፈር ልሶ እንዲዋጋ ሲያስገድዱ፣
በት.ዲ.ኤፍ ውግያ ስልት የወራሪ ሃይሎች በረገዱ፣
ትግራይ ሳይወጡ በት.ዲ.ኤፍ (TDF) መብረቃዊ እርምጃ ነደዱ::
የኢትዮዽያ አየር መንገድ ትግሬዎችን በትግሬነታቸው ከሥራ አባርሮ፣
ወታደሮችና መሳሪያ ለትግራይ ጀኖሳይድ ሲያጏጉዝ ተባብሮ፣
ሲ.ኤን.ኤን ሲያጋልጠው በመግለጫ ለመካድ ሞክሮ፣
አየር መንገዱ ተኮነነ በምስሎች ተመስክሮ::
ፕረዚደንትዋ ወደ መቀሌ ለጉብኝት፣
የፆታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ለማየት፣
የዘበኞቻቸው ወታደሮች ባይገቡ ዶክተሮች ሲሰጡ አስተያየት፣
እኔ ሳህለ ወርቅ ካለ አጃቤ አልገባም ብላ ያለእፍረት በድፍረት፣
ፕረዚደንትዋ በጭካኔ ከነወታሮችዋ ገባች ወደ ሴቶች ቤት፣
የተበደሉት ሴቶች ሲያዩ የፕረዚደንት ወታደሮች ኡይ አሉ በጭሆት፣
ለሁለተኛ ግዜ በፕረዚደንትዋ ተደፈሩ በአእምሮ ቁስለት::
የቲ.ዲ.ኤፍ (TDF) ደባይ ስልት መሮዋቸው ሳይቻቻሉት፣
አረሜናዊ ተግባራቸው ለመሸፈን ቀየሱ የውሸት ትርክት፣
ገበሬ እንዲያርስ ለጥሞና ወጣን ብለው ሰጡ ምክንያት::
በቁጥሩ የበዛ ምርኮኛ ስታይ በመቀሌ፣
ሰራዊቱን ክዶ ፎቶ ሾፕ ነው አለ ባጫ ደበሌ::
ዐብይና ብልፅግና በውግያ አናሸንፍም ብለው ግምገማ አደረጉ፣
የኢሳያስ ሴራ ተበድረው ትግራይ በከበባ ዘጉ፣
የረሃብ ሞት በትግራይ ህዝብ ላይ ደነገጉ::
ዐብይ በህግ እንዳይጠየቅ ንጉሥነቱ ለማስረዘም ሲራመድ፣
ኢትዮጵያ እንድትፈርስ እሳት ሲያጉድ፣
ጀኖሳይድ ፈፅመህ አይቻልም በነፃ ለመኖር፣
የግዜ ብቻ ነው ፍትህ የማይቀር::
የትግራይ ህዝብ ሌላ ስልት እንዲነድፍ እንደገና ተገደደ፣
የትግራይ መንግስት ለሰላም ቅድሚያ ወሰደ፣
ዐብይ ከአፍሪካ ህብረት ተባብሮ ለሰላም እንቅፋት አቀደ፣
በውሸት የኢትዮዽያ ህዝብ እያታለለ፣
ሰላም እያለ ህዝብ እየገደለ፣
ዐብይ ተጠያቂ እያለ፣
ኢትዮዽያ እውነተኛ ሰው አጣች ተባለ::
የዐብይና የኢሳያስ ወታደሮች ሳይወዱ አስረከቡ የታጠቁት፣
ዐብይ ያጋጠመው የመሳርያና የገንዘብ እጥረት፣
የውሸት ዲፕሎማሲው ልመና ወደ አሜሪካና አውሮፓ ህብረት፣
የትግራይ ጦርነት ሳታቁም አንሰጥህም አሉት ረዲኤት::
የአማራ ፅንፈኛ ዋናው ህመሙ የትግራይ መሬትና ታሪክ ነው ለመውረስ፣
በውሸት ትርክት በማድበስብስ፣
ሐቅ ተቀብሮ አይኖርም ለዘለዓለም፣
የኢትዮዽያ ሥልጣኔና ግዕዝ የፈጠረው ትግራዋይ ነው በአክሱም::
የአማራ ሊሂቃን፣ ዻዻስትና ቀሳውስት፣
ጥላቻ ሰነቆው ትግራይን ለማጥፋት፣
ህዝቡን በሰይጣናዊ ፖለቲካ ሰበካ አናወጡት፣
መሬትና ታሪክን ለመቀማት፣
ጁንታው [ትግራይ ህዝብ] ከሚገዛን ብሎ ድያብሎስን መረጡት::
የአማራ ፅንፈኛ በህግ አልባነት የሚመራ በኢሳያስ የሚነዳ፣
ለሆዱ ሲል ሀገር ሲከዳ፣
ንፁሃን ገድሎ ንብረትን ዘርፎ ወደ ጎንደር ሲወስድ፣
የቲ.ዲ.ኤፍ (TDF) ድምፅ ሲሰማ ልቡ የሚርበደበድ፣
ሲማረክ እንደ ጀነራል ጨመዳ በፍርሃት ሲርበደበድ
ሱሬውን በሽንት አጥለቅልቆ ጀግነቱ ሲዋረድ::
የአባይ ግድብ በትግሬ ጥረት የተጀመረ፣
የአማራ ፅንፈኛ በሁለት ቢላ መብላት ተዋፈረ፣
ከግብፅና ከኤርትራ ተባባሪ ሆኖ ግድቡ እንዳይሠራ ሴራ ጫረ፣
ሃጥያቱን ሳይናዘዝ ውሸቱን እያሰራጨ በአረሜነቱ ተሰማረ፣
ህዝብን እያደናገረ አሁን ግድቡ የኔ ነው ብሎ ተናገረ::
ኢሳትና (ESAT) ኢትዮ 360 የውሸትና የጥላቻ ዘመቻቸው በህወሓትና ትግራይ ሲነዙ ያለ እረፍት፣
የአማራ ህዝብ ትግራይን እንዲጠላ መረዙት፣
የትግራይ ጀኖሳድ እንዲቀጥል ዐብይን አመጎሱት፣
ግዜ ሳይወስድ የዐብይ አህመድ መደመር አበቃ በግጭት፣
ዐብይ ተነሳ የአማራ ፋኖ ትጥቁን ለማስፈታት፣
ኢትዮ 360 ጋዜጤኞች ፀረ ዐብይ ሲነሱ በጭሆት፣
ሃብታሙና እርምያስ ምላሳቸው አጥፎው የኢህአዴግና ህወሓት አስተዳደር ይሻላል በማለት፣
“የአፓርታይድ ሥርዓት በአዲስ አበባ” ብለው ዐብይን አወገዙት በምሬት::
የትግራይን ህዝብ ኢትዮዽያን ጠብቆ የኖረ በዋልታው፣
ኢትዮዽያን የመሰረተና ባጎረሰ እጁን የተነከሰው፣
ይህን ሁሉ ግፍና ክህደት ሲደርስበት ማን አለ ተው፣
ሀገር እንደ ሀገርነት መቀጠል የምትችለው፣
ለተገፋ ህዝብ ስትደርስለትና ስታወግዘውለት ሰቆቃው፣
አልያም ሀገር ትፈርሳለች በዐብይ አረሜኔው፣
የኢትዮዽያ ህዝብ ሆይ ለምንድነው ዝምታው::
ሰላም አይመጣም በደሉን ከልብ ታምኖ በይቅርታ ሳይካስ፣
ከበባ ሳይከፈት፣ ሰብአዊ አገልግሎት ሳይመለስ፣
እውነትን የጎደለበት ሰላም ከመጀመሪያው ድረስ ፣
የአፍሪካ ህብረት ኤርትርያ ከመኮነን ወደ ሰላም እንድትገባ ደነገገ፣
የተጠበቀው የሰላም ድርድር ሳይጀመር እንዳይሳካ እየተደረገ፣
የትግራይ ህዝብ ሆይ ወደ አክሱም ግዛትህ ተመለስ ነገ::
የትግራይ ህዝብ እንደ ባዕዳዊ ተቆጥሮ፣
የትግራይ ህዝብ ባንክ ሂሳቦች ኣጉሮ፣
“የዮሃንስ ልጆች ገንዘብ እንዳያገኙ አድርገናል” አለ ዐብይ አማርሮ፣
በእንዴት አኳሀን ነው የትግራይ ህዝብ ከኢትዮዽያ ጋር እንዲኖር አብሮ?
ከእንግዲህ ወድያ መለያየት ነው በብዕርና ድምበር ተሰምሮ::
Mentioned what all done on the Tigray people and I really apprciate you.