ሰማይ ሰማያቱን በረራ
መጣሁን ዘልቄ ሰሜን ተራራ
ጎጃም በራንዳ እህል ተራ
ላሠራጭ የማከብረው ሥራ::
ስሜ የውሽት ጎተራ
ትውልዴ ጋይንት አማራ
ሱስ አለብኝ ሕይወቴን የሚጋራ:
አንደኛው ጉራ
ዳግምኛው ሲወራ
ባልነግረው ቢሻል ነበር
ኣዳሜ ከሚፈራ::
እንደ ዳሜራ:
እሳት የሚዘራ::
መሬት:
በደም ማጨቀየት:
ሰው ኣርዶ እንደቅጠል:
ማቃጠል::
ዘር ግንድ የለኝ ተነግሮ ሚጣራ
የራስ ታሪክም የሚያኮራ
ባህል በለው ከሰው እምጋራ::
ምን ይዤ ልምጣ ምንስ ላውራ:
ለዚህ ነው የሆንኩት ደብተራ::
የተማርኩትም ጥንቆላ
ሥራዪ ከዚያ በኃላ
ትንግርት ፈጠራ
ሌት ተቀን የሌለ ሓቅ ሳወራ:
የውሽት ግንብ ሥስራ::
በሌለ ሃገር ስፈነጥዝ ስኮራ
በሌለ ፍቅር ስጣራ
ሳውለበልብ እረንጏዴ ብጫ ቀይ ባንዴራ
ስንጠራራ ያዙኝ ልቀቁኝ ፍኮራ::
ኣታለልኩኝ ብዙዎች ሲራራ
ለሞቶ ዓመታት ጠላት በለው ባለንጀራ
ባደባባይ በለው እልፍኝ ጎራ
ሌሊቱን ሳጎራ
የሴት ስብስብ
ሳሻ ስድርዝ በየተራ
ወፍራም አይቀር ዒባራ
መልከመልካም በላት ኩታራ
ይህ ነው እኔ ማለት ኣማራ
ሓቁን በግልፅ ሲብራራ::
ያሬድ ሑሉፍ