ቁርሱ ጠርሙዝ ሙሉ ደም ፈሳሽ: ጉዱ ሲመሳሽ!

News

ምን ታኣምር
እግዜር የተጣላው ዘር
ራሱን ጤና ነፍጎ
ሌላውን የሚያስቸር::

ምኒን ጨብጦ
ምን ይልቀቆ
ይብቃኝ የማያቅ
ያየው ሁሉ የሚናፍቅ::

ኣንትም ኣንቺ
እሲም እሱዋም
ይህቺም
የኔ ንብረት
ቢክዱ ክ
ቢሉም ኣሻፈረኝ እንጃ
ኣለኝ ኣስተማማኝ ማስረጃ
ውሉ ስነዱ
የተፈረበት በጃኖሆይ ግምጃ::

ምን ተናግሮ
ምኑን ይደብቅ
ስስቱ ገደብ የለሽ
ስወራጭ ግራና ቀኝ
እንደተለከፈ እብድ ውሻ
መነሻው ኣያውቅ መጨረሻ
ኣጠገቡ ለቆመ
ስው ይሁን እንስሳ
ጥርሱን እየሸከለ ስላም የሚነሳ::

ኢትዮጽያ ለኢትዮጽያውያን
የማንም ሳትሆን የማን
ባድ ለቆመላት እናት
እያለ የሚጮህ ሲያቅራራ
ዳሩ ግን ካልሆኑ ዓማራ
ከሃገራቸው እንዲረሩ ሳይራራ
ቤት ንብረቸው እየዘረፈ
እየገደለ እየጨፈጨፈ
ድንበር መሬታቸው
ዓማራ ነው እያለ እየከለለ
ይመፃደቅ ጀመር
እትንኩኝ እያለ
ሲሻው ገድሎ እየሸለለ::

ኢትዮጽያዊ ነኝ
ብሎ ሲመፃደቅ
የተፉው ምራቁ ሳይደርቅ
ኣኩሪ ዓማራነተን ይላል እንዲታወቅ
ሁተት ተቃራኝ ኣቃም የማይታረቅ::
መያዣ ያጣ ዝብርቅርቅ
የእብድ ፈሊጥ ድብልቅልቅ::

እስቲ ምንይባላል
ይህ ኣይነት ኣዙሪት
ዳቦውን ፈልጎ
ምጣዱን መከርበት:
የእብደት እብደት
ከልክፍት ውሻ
ህመሙ እጅጉን የጠናበት:
መድሃኒ ቢፈለግ ቢፈለግ
በዱር በገደሉ
መዳውም ቢዳሰስ
ኣዳኝ እፃዋት ፈውስ
በግር በፈረስ
ዘውድ ያጠለቀ ቃኘውም ጨምሮ
ቢጋልብ ኣምርሮ
ሥር ስደድ ዘር በከል በሽታ የኣእምሮ
ተጠናውበት ውሎ ኣድሮ ጠንክሮ
መድሃኒት መቸ ሊግኝለት ዘንድሮ::
የኣይጥ ምስክርዋ
ድቢጥ እንዳሉት
ጥጋብ የቅርብ ጔደኛው ቅሌት
እብደት ኣብሮት የሚያድር ሞት:

ቁርሱ ዳቦ ከመብላት ቁራሽ:
ጠርሙዝ ሙሉ ደም ፈሳሽ:
ጉዱ: ሲመሳሽ ብርሌ መርዝ
ኣንጀቱን እንዲያሽ::

እንግዲህ መፍትሄው
ኣንድና ሁለት
ለኣንባቢው ልተውለት
ይለይለት::

ተመስገ ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *