የበቀለ ልጅ….!
ዘመድ የለ ፈጥኖ ደራሽ
የሚያበረታታ የሚል ኣይዞሽ
በተዘጋ ቤት ፍርስራሽ
ውሀ የለ ሚበላ ቁራሽ
መኖር ግድ ሆኖ ሥጋ ለባሽ:
ቀን እስኪያፍ እስኪመሻሸ:
ባለኣደራ ኣትክልት: ማሙሽ
ባፈራ እንዴት ደስ ባለኝ : ደም መላሽ::
ይሄው ለዓመታት ስመኝ
ሳይታክተኝ ሳይደክመኝ
ምን እለ ቢያድለኝ
ለተከፍው ልቤ!
ማፅናኛ ደብዳቤ:
ጌታ ልጅ ቢስጠኝ:
ከሚታመን ጏድ ከሚወደኝ
ኣለሁ ባይ ሲከፋኝ:
ደስታዬም ተካፍይ :
ልጅ ካለም ተንከባካይ::
በዓለም ከዚህ በላይ
ምን ኣለ ሌላ ንዋይ::
ታድያ ስኖር ስንገላታ
ስወጣ ስወርድ በርካታ
ካሳስብኝ ሁኔታ:
መለስ ብሎ ጌታ!
ተስፋ እንዳልቆርጥ እንድበረታ:
ስመፕው ውሎ ያደረ:
ለገሠ: ባለውለታ ባል: ወረወረ:
መህፀኔም ቆጠቆጠ መሀን ሁኖ ኣልቀረ:
የበቀለ ልጅም: ስመፕው ተባለ::
አድጎም ከተማረ
ለተጠማው ሁሉ: ኣንጀቱ ላረረ
አጥቶት ለነበረ
እጅ ስነዘረ:
ውሀ : ምግብ ላቀብል ኣለ
ጉልበት እስከቻለ::
መሳቅ ኣይሉት ገደብ የለሽ ሳቀ
ፍፁም በደስታ ልቤ ፈነደቀ:
ፍትሕ መሬት ላይ ፀደቀ::
በዚያው ልክም ምቀኛ ፈለቀ
ከወሀ ጥም ድሀን ላላቀቀ
ወነጄለው ጉሮሮው እንዳደረቀ:
እርር ድብን ብሎም በንዴት ደቀቀ:
ግራ ቅኝም ተቻኮለ
ልጄን ሊያጠፋ ምን ግዜ ኸጀለ::
ታድያ በጠማማ አእምሮ
ኣምባጏሮ ጭሮ
ንፁሃን ገደለ ልጄንም ጨምሮ::
ላያልቅ የኔ እሮሮ!
ወይ ዘንድሮ!
መቼ ያልቃል ተነግሮ
ቀማኛ ካልተመቸው ኑሮ
አቅመ ቢሱን ስባብሮ
ልበ ቁኑን አጭበርብሮ
ሁሉ እንዲጠፋ ተበነቃቅሮ
ይራራጥ ጀመረ በአስተክሮ:
የአህያዋን ምሳሌ ተክትሎ:
“እኔ ከሞትኩኝ በኃላ
ስርዶ አይብቀል እንኻን የሚበላ”::
ያሬድ ሕሉፍ
20/03/2020
http://togoruba.org/togoruba1964/mainTogorubamap/mainMap/headingMap/2020/2003YH20-03PT.pdf