ውቤ በረሃ!
ስው ጠፍቶ ስሙ የሚጠራ
ቅን በተግባር የሠራ
ውቤ በረሃ ኣሉት የከተማ ቦታ
ሲያደንቁ ወሮበላ ሽፍታ።
የጤና ቀውስ የኣዕምሮ ኣዝሮሽ
ከተማን ገንብቶ በረሃ መሞረሽ
ስላምን ተርቦ ጠብን መቆደሽ።
እኚህ ኩታራዎች የታሪክ ኣተላ
ግፍ መፈፀም ኣልበቃ ብሎ
ወንበዴን ወደሱ
ቀደሱ ኣስመስሎ።
እርኩስ ዲቃላ
ከእግዚሔር የተጣላ
ቅይጥ የሰይጣን ባቂላ
የወንድሞቹን ደም የጠጣ
እንደጠላ
የንፁሃን ሥጋ ኮምኩሞ የበላ
ኣጥንት የሰበረ እንደሸክላ
ለምን ቢባል የወንበዴ ሜላ
መግዛት ነው ቀጥቅጦ በብረት በዱላ።
ይህ ሲሆን የትላንቱ ልምድ
ዓለም ወደፊት ስትራመድ
እኚህ ቅዤታሞች
እንደገና ብረት ኣንግተው
ሽፍትነት ለማንገሥ
ኣሁንም ደግመው
ጀመሩ ቀና ጎንበስ።
የተረገመች ይህች መሬት
በተለይ በተለይ ኣሉ ሦወሥት ኣሁጉርት
ራሻ ኢስራኤል ኢትዩጵያ ሚባሉት
እሾኽ ኬላ
እግር ሚባላ
እንደጉንዳን ሚፈላ።
ኣሁን ደግሞ ልንሰማ
ማን ብለው ሊጠሩት
ይሆን ኣዲሱ ከተማ
የቆመው በኢመሬት/UAE ድጎማ?
ተመስገን ኸበደ