እሪ በከቱ፣ ደሮ ማነቅያ!

News

እሪ በከቱ፣ ደሮ ማነቅያ!

ኣለ ኣሉኝ ሃገር
ብረት ተሸክሞ ማዕገር
ከተማ ላይ ታች መንጎራደ ድ ሲያምር
ሚቆጠር እንደክብር
እምያስፈራ ጠላት ስይኖረው
እንዳሉ ኣስመስሎ ሚከምር
በሆነባልሆነ እድር
ስርግይሁን ቀብር
ጥይት ሚፈነጅር
ኣስመሳይ ሎሌ
ቀልደኛ
ስው ሲበደል ሲጮህ ክፉኛ
እሪ በከንቱ ኣውቆ ሚተኛ
ጆሮው እንዳልስማ
መሃል ከተማ

ብሎም መነሃርያ
ቢጮህ ደሙ ፈሶ ማለቅያ
ጠበንጃው እንጋቢ ዘብጥያ
ዘብ ቁሞ ንጉሡ ቤት ዙርያ
ስው ሊያድን ቀርቶ ከጅብ ጋያ
መንደሩ ሆነ ደሮ ማነቅያ።

በላይ ኣምበላይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *