ዓድዋ የት ነሽ እኮ?

News

ዓድዋ የት ነሽ እኮ?

ዓድዋ ላይ እኮ ነው ዓድዋ
መንገድ ተጉዞ ማን ወሰደው ሽዋ
ስሚቶ ኣይደለ ኣሸዋ
በካምዩን ተጭኖ
ለይስሙላህ ኣዳራሽ ሊሠራ መጠርያ ለሥምዋ:
ያልታደለች ዓድዋ
በጦር የቆሰለች ፅዋ
መሳለቅያ
በኣንኮበር ዙርያ::
ቱሪስት መናሃርያ::

ሲሸልልሉ ቢውሉ ዓድዋን ሲዘክሩ
ጉራዴ ጠመንጃ እየሰነዘሩ
ዓድዋ ኣደባባይ ላይ እየተሽከረከሩ
ዓድዋን ሳይሆን የሚጠሩ
የፈለጉት ምስጥሩ
ሌላ ነው ነገሩ
ሥም ሊጠሩ
ምኒልክን ሊያከብሩ
ውሸትምስክሩ
ባልዋልበት ሜዳ ሲተረተሩ::

እንካን ጦር ሊሸከም
ጠመንጃ እርግጫሊቃቃም፣
ሊጋልብ ድሩ ሸንተረሩ
ቆፍጥኖ ማይራመድ ማይችል በግሩ፣
ከካሣ ኣባ በዝብዝ ሊያወዳድሩ
ያልተስራ ታሪክ እንደለመዱት ውሸት ሊያወሩ።

ዓድዋ የጦር ፅዋ
መሳለቅያ ሆነ ሞካንንት የሸዋ
ግዛት ሊያስፉፊ ከሞያሌ እስከ ማሣዋ
ምርኩስ ተደግፈው ረዥም ግራዋ
ሲንገዳገድ ወድቆ የጣለው ያ ወልዳማ
ኢሳያስ ኣውራ ደሮ ሳዋ::

ተመስገ ኸበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *